በለንደና አካባቢው ለምትገኙ ዉድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስልን::
በዚህ በመዲናችን ለንደን ከተማ በየአመቱ የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈው የሎንደን ማራቶን የፊታችን እሁድ 28 April 2019 ከጧቱ 9:05am ጀምሮ ይካሄዳል። በመሆኑም ሁላችንም አትሌቶቻችን በቦታው በመገኘት እንድደግፍና አሁን የተጀመረው የአብሮነት እና አብሮ የመስራት መንፈስ አትሌቶቻችንን በድጋፍ ልናሳይ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በፅኑ ያምናል ።
ስለዚህ ሁላችንም በቦታው በመገኘት ድጋፋችንን እናሳይ እያልን የሩጫው መነሻ ብላክሂዝ ግርንኢች ፓርክ ሲሆን ፍፃሜው ደግሞ ዘ ሞል ባኪንግሃም ፓላስ ይሆናል ነገር ግን የሩጫው መዳረሻ ቦታዎች ሁሉ ከታች ይጠቀሳሉ። ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ምስጋናችን ከወዲሁ ከፍ ያለ ነው።
የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ብሄራዊ ኩራታችን የሆኑት አትሌቶችን መልካም እድል እየተመኘን በድል እንደምትመለሱ መሉ ተስፋ አለን::
የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ዩኬ
The world famous London Marathon will take place this Sunday 28 April 2019 at 9:05am. The Marathon stating point is Blackheath, Greenwich Park and will finish at The Mall, Buckingham Palace. Ethiopian Sports and Culture Federation would like to take this opportunity to call all Ethiopians to come out and support our proud athletes in order to show our unity.
Some of the viewing points on the route are: Tower Bridge, Isle of Dogs, Canary Wharf, London Bridge, Embankment, Parliament Square, Birdcage Walk and the finish will be on the Mall in front of Buckingham Palace.
Ethiopian Sports and Culture Federation UK wishes all the best to both Ethiopian and British athletes.
Ethiopian Sports and Culture Federation UK